ራዕይ እና ተልዕኮ

ራዕይ እና ተልዕኮ

ራዕይ

   ለትውልድ መሪ የሆነ ዓለም አቀፍ የእውቀት ማዕከል ለመሆን የሚሰራ፣ በሃገራችን ተፎካካሪ፣ ብቁ፣ ውጤታማ እንዲሁም በባለ ሙሉ ስብዕና ዜጎችን የሚያፈራ ብሎም በሁለተኛ ደረጃ፣ በመሰናዶ እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ስርዓተ ትምህርት ውስጥ የሃገራችን ብሎም የምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም ማዕከል መሆን ነው፡፡

 ተልዕኮ

·       ውጤታማ፣ ተፎካካሪ እና ኃላፊነት የሚሠማቸው ተማሪዎችን ማፍራት፣

·       መሠረታዊ እና ተግባራዊ የሆኑ ትምህርቶችን ለተማሪዎቻችን በጥራት ማስተማር፣

·       ጤናማ የሆነ የትምህርት ቤት ገፅታን በመፍጠር ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ሠራተኞች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፣

·       የስነ ልቦና እና የሞራል ድጋፍ ግልጋሎቶችን መስጠት፣

·       ጠንካራ መሰረታዊ ስርዓተ ትምህርትን የተከተለ ትምህርትን መስጠት፡፡

ግብ

·       ተማሪዎች ለቀጣዩ ህይወታቸው መሠረት የሚጥሉበት እና አዲስን ነገር የሚቀስሙበት ዋነኛ ማዕከል ትምህርት ቤት በመሆኑ ለተማሪዎች ተጨማሪና ልዩ እገዛ የሚሰጥበትን አሠራር መዘርጋትና መተግበር፤

·       የመማር ማስተማር የስራ ሂደት ከምንም በላይ በቂ የተማረ የሰው ኃይል አቅርቦት የሚፈልግ በመሆኑ ብቃትና ልምድ ባላቸው መምህራን ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጥ ማድረግ፤

·       ምቹ የሆነ የመማር ማስተማር ከባቢን ለመፍጠር ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን መገንባት፣

·       ደረጃቸውን የጠበቁ የንባብ ማዕከሎችን ማደራጀት፣ የተግባር ትምህርት መስጫ ማዕከላትን ማደራጀት፣

·       ከዚህ ቀደም የነበሩንን የአሰራር ስልቶች እና አተገባበሮች ላይ ጥናት በማድረግ ለተልዕኳችን እውንነት እገዛ ሊያደርጉ የሚችሉ አሠራሮችን እና ባለሙያዎችን ተሣታፊ ማድረግ ብሎም አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ፤

·       ተማሪዎቻችንን በአገር አቀፍ ፈተናዎች በከፍተኛ ደረጃ ውጤታማ ማድረግ፡፡